Comments
Description
Transcript
C2.0 2 1 /
C2.0 ሂሳብ 6 የወላጅ መገልገያ 2ኛ ማርክ መስጫ ወቅት: የቁጥር ዝምድናዎች የማርክ መስጫ ወቅት 2 ከዚህ በታች የተዘረዘሩ 6 የትምህርት ርእሶችን ያካትታል። ይህ መገልገያ ለ5ኛ ርእስ ነው። 1 ኛ ርእስ 2ኛ ርእስ 3ኛ ርእስ 4ኛ ርእስ ባላበርካታ ዲጂት /መደብ ስሌት ( ዴሲማሎችን ማባዛትና ማካፈል ) የቁጥሩን መስመር ማራዘም ስርአትና ፍፁም ዋጋ የማዋያ ዝምድናዎች (Absolute Value) (Coordinates) 6ኛ ርእስ ኤክስፖኔንቶች የመማር ግቦች በጋራ ዋነኛ የስቴት መመዘኛ ርእስ ባለ በርካታ ዲጂት/መደብ ስሌት (ሙሉ ቁጥሮችን ማካፈልና የዴሲማል ግብረቶች) 5ኛ ርእስ ባላበርካታ ዲጂት/መደብ ስሌት (ሙሉ ቁጥሮችን ማካፈልና የዴሲማል ግብረቶች ) ተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት በቀልጣፋነት ባለበርካታ-ዲጂት ቁጥሮችን ማካፈል በመደበኛ ቀመር በመጠቀም። በቀልጣፋነት ባለ በርካታ-ዲጂ ዴሲማሎችን መደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛት እና ማካፈል - ለያንዳንዱ ግብረት በመደበኛ ቀመር በመጠቀም በላይኞቹ ሀይፐርሊንኮች ውስጥ የሚገኙ ትምህርታዊ ቪድዮዎች የC2.0 ይዘት እንዲደግፉ የተተለሙ ናቸው፣ ሆኖም MCPS ትኩረት በማያደርግባቸው የቃላት ዝርዝር ወይም ስልቶች መገልገል ይችላሉ። የጋራ ዋነኛ የስቴት መመዘኛዎች ከባድ የሂሳብ ግኝት በሚያስከትሉ ሚዛናቸውን የጠበቁ ሶስት መሰረታዊ አካሎች ይጠይቃል፡- ጥልቅ ፅንሰሀሳባዊ ግንዛቤ፣ የቅደም ተከተል ተክእሎ፣ እና የሂሳብ ትግባሬና የሞዴል ዝግጅት። RIGOR ባላበርካታ ዲጂት /መደብ ስሌት ( ሙሉ ቁጥሮችን ማካፈልና የዴሲማል ግብረቶች ) ጥልቅ ፅንሰሀሳባዊ ግንዛቤ በመደበኛ ቀመር በመገልገል ባለበርካታዲጂት ዴሲማሎችን አቀላጥፎ ለማባዛትና ለማካፈል ተማሪዎች በተመጣጣኝ ክፍልፋዮች እውቀት ይጠቀማሉ። የቅደም ተከተል /ስርአት ተክህሎ ባለበርካታ-ዲጂት ሙሉና ዴሲማል ቁጥሮች በመደመር፣ በመቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል ተማሪዎች ፍጥነትና ትክክለኛነት ያዳብራሉ። ትግባሬዎችና የሞዴል ስራ ተማሪዎች በተጨባጩአለም አውደንባብ የሚገኙ ፕሮብሌሞችን ለመፍታግት የመደመርን፣ መቀነስን፣ ማባዛትና ማካፈል መደበኛ ቀመሮችን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs - Amharic C2.0 ሂሳብ 6 የወላጅ መገልገያ 2ኛ ማርክ መስጫ ወቅት: የቁጥር ዝምድናዎች 5ኛ ርእስ ባለበርካታ-ዲጂት ስሌት (ሙሉ ቁጥሮች ማካፈልና የዴሲማል ግብረቶች ) የመማር ተሞክሮዎች በጋራ ዋነኛ የስቴት መመዘኛ 5ኛ ርእስ ባለበርካታ-ዲጂት ስሌት (ሙሉ ቁጥሮች ማካፈልና የዴሲማል ግብረቶች) ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... ቤት ውስጥ፣ ልጅዎ ማድረግ የሚችለው/የምትችለው... በተጨብጭ-አለም አውደ ንባብ ውስጥ ለቀረቡ ፕሮብሌሞች ተገቢ ግብረቶችን መምረጥ። ለፕሮብሌሞች መፍትሄዎች መገመት። በተሰጠ ፕሮብሌም የስሌት መፍተሄዎችን መለየት። በመደበኛ የስሌት ዘዴ በመገልገል በለበርካታ-ዲጂት ዴሲማሎችን መደመርና መቀነስ። በመደበኛ የስሌት ዘዴ በመገልገል ባለበርካታ-ዲጂት ዴሲማሎችን ማባዛትና ማካፈል። የተወሰነ ርቀት ለመራመድ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መወሰን o የዩናይትድ ስቴትስ አግድም ስፋቱ በግምት 3935 ማይሎች ነው። ዩናይትድ ስቴትስን አቋርጦ ለመራመድ ማን ያህል ግዜ ይወስዳል (መካከልኛ ሰው በአንድ የ8 ሰአት ቀን 20 ማይሎች መራመድ ይችላል)? o የመሬት መጠነ ዙርያ 24,901 ማይሎች ነው። የአለምን ዙርያ በእግር ለመጓዝ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል (መካከልኛ ሰው በአንድ የ8 ሰአት ቀን 20 ማይሎች መራመድ ይችላል)? o ሌላ ቦታ መምረጥ፣ ርቀቱን ተመራምሮ ማግኘት፣ እና ያንን ርቀት በእግር ለመጓዝ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መወሰን። በገንዘብ መስራት o የመንገድ ዳር ሽያጭ ማስተናገድ፣ የተጋገረ ሽያጭ ወይም ለስላሳ መሸጫ መድረክ። የእያንዳንዱ ደንበኛ ጠቅላላ ሂሳብ ማስላት (ዴሲማሎች እየደመሩ) እና መልሶች (ዴሲማሎች በመቀነስ)። o የተለያዩ መጠኖች/ብዛቶችን ለመግዛት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚጠፋ መወሰን። o ከአንድ ምግብ ቤት ማስከፈያ ቢል የያንዳንዱን ሰው ድርሻ መወሰን እና በ15% ወይም በ20% ሂሳብ ጉርሻ ማስላት። በአንድ የቁጥር አረፍተነገር ውስጥ የጎደለው የዴሲማል ነጥብ የት መግባት እንዳለበት መወሰን፡o o 31.61 5.8 545 (ትክክለኛው መልስ 5.45 ነው) 326872 36.4 8.98 (ትክክለኛው መልስ 326.872 ነው ተጨማሪ ልምምድ በተጨባጭ አለም ውስጥ ፕሮብሌሞችን መፍታት Interactive Practice (ግጥምያ) MP1 ርእስ 4 ባለበርካታ-ዲጂት ስሌት (Flexbook) MP2 ርእስ 1 ባለበርካታ-ዲጂት ስሌት (Flexbook) የተጨማሪ ልምድ አገናኞች (links) የC2.0ን ይደግፋሉ፣ ቢሆንም MCPS የሚያተኩርባቸው የቃላት ዝርዝር ወይም ስልቶች ባይሆኑም ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs - Amharic