...

የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና MT የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት

by user

on
Category: Documents
16

views

Report

Comments

Transcript

የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና MT የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና
ማርክ መስጫ ወቅት 1፣ ክፍል 2
MT
የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት
(Learning Goals by Measurement Topic - MT)
ተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት ...
 የመረጃዊ ጽሁፍ ዋና ሃሳብ መለየት ።
መረጂያዊ ፅሁፍ

የተለያዩ ጽሁፍ ባህርያትን መለየትና መጠቀም።
 ተመሳሳይ ርዕስ ያላቸው የሁለት ጽሁፎች ጠቃሚ ነጥቦችን
ማወዳደር።
 ማን፣ ምን፣ መቼ፣ የት፣ ለምን እና እንዴትን በመጠቀም
መጠየቅ እና ጥያቄዎችን መመለስ።
ቋንቋ፡ የቃላት
ዝርዝር
 ለቃል ወይም ሀረግ ትርጉም በአረፈተ ነገር-ደረጃ ያለ ሁኔታን/ጉዳይን ፍንጭ/መነሻ አድርጎ መጠቀም።
 መረዳትን ለማብራራት፣ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ ወይም አንድን ርዕስ በጥልቀት ለመረዳት ተናጋሪው/ዋ
ያለው/ችውን በተመለከተ መጠየቅና ጥያቄዎችን መመለስ።
 በተመሳሳይ ስር ለሆነ ያልታወቀ ቃል ትርጉም የታወቀን ስር ቃል ፍንጭ/መነሻ አድርጎ መጠቀም።
አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች
(Thinking and Academic Success Skills -TASS)
ትብብር
የቋንቋ
ቅልጥፍና
ይህም...
ለአንድ ፕሮብሌም ወይም
ሃሳብ በርካታ ምላሾች
ማመንጨት።
በንባብ ተማሪዎች የሚያደርጉት...
 ስለ አንድ ጽሁፍ የተለያዩ ቀላልና ውስብስብ ጥያቄዎችን መጠየቅ።
 ክፍት ማለቂያ ለሌላቸው/ላልተገደቡ ጥያቄዎች በተለያዩ መንገዶች መልስ መስጠት፣
በቃል ወይም በፅሁፍ።
 ያልታወቁ ቃላትን ትርጉም ለማግኘት በተለያዩ ስልቶች መጠቀም።
የቡድን ግብ ለመምታት
 በጋራ ውይይቶች (ከአንድ ጽሁፍ የተማሩትን አዲስ መረጃ ለመወያየት በጥንድ ወይም
በውጤታማነትና በመከባበር
ትንሽ ቡድኖች አብሮ በመስራት) መሳተፍ።
መስራት።
 የሌሎችን አስተያየቶችና ሃሳቦች ማክበር።
 እንድ ግብ ለመድረስ ወይም የገቢር ፕላን ለማከናወን ሀላፊነቶችን መጋራት።
 በርካታ ሃሳቦችን ለመጋራት እና ለማዳመጥ ፈቃደኛነት ማሳየት።
በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ
ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional
Programs
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና
ማርክ መስጫ ወቅት 1፣ ክፍል 2
የመማር ተሞክሮዎች በመለኪያዊ አርእስት
(Learning Experiences by Measurement Topic - MT)
ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ...
MT



የተለያዩ ዲጂታልና ህትመት መገልገያዎችን ማንበብና ማወዳደር።
ደረሲዎች ምክንያቶችንና ምሳሌዎችን በመጠቀም እንዴት ጉዳዮቻቸውን
አንደሚደግፉ መወያየት።
የተለያዩ የጽሁፍ መለያዎችን በመጠቀም ስለ ጽሁፍ መጠየቅና ጥያቄዎችን
መመለስ።
በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ...

ሁልቀን አንብቡ። አቀላቅሉት! ትረካዎችን፣ መረጃዊ መጻሕፍት፣ የምግብ ባልትናዎች፣
መፅሄቶች፣ ዲጂታዊ መገልገያዎች፣ ወዘተርፈ ማንበብ።
* መማርን የሚያግዙ በቀጥታ በኮምፒውተር ያሉ መገልገያዎችን ለማግኘት የትምህርት ቤትህ/ሽ/ን
ድርጣቢያ ተመልከት/ች*
መረጂያዊ ፅሁፍ
እርምጃን መቀጠል፡ ስለ መረጃዊ ጽሁፍ ማሰብ
 አንድን ጽሁፍ የበለጠ ለመረዳት እንዴት የጽሁፍ መለያዎች ሊያግዙህ/ሽ
ይችላሉ?
 ከካርታው ምን መረጃ ለመማር ትችላለህ?
 ርዕሱ/አጭር መግለጫው ስለ ስዕሉ ምን ነገረህ /ሽ?
 የቃላት ማጣቀሻው ከይዘት ማውጫው እንዴት ይለያል?
 ርእሰ አንቀጾች የምትፈልገ/ጊ/ውን መረጃ ለማግኘት እንዴት



ቀልጣፋ አንባቢ መሆን፡
ልጅዎ የታወቀ ጽሁፍን በንባብ ጥራት፣ ትክክለኛነት እና አገላለጽ ላይ በማተኮር በርካታ
ጊዜያት (ሶስት ጊዜ ቢሆን ይመረጣል) እንዲያነብ ይገፋፉ።
ለልጅዎ የቀልጣፋ ንባብ ምሳሌ ይሁኑ።
አንድ ምንባብን ጮህ ብሎ የሚነበብበትን ጊዜ በመያዝ የቀልጣፋ ንባብ ጨዋታ ይስሩና
ልጅዎ የራሱ/ሷ/ን ጊዜ ለማሻሻል ይሞክር/ትሞክር
ይረዱሃ/ሻ/ል?
አጭር
መዝገበ
ቃላት
ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር


የታወቀ ስር ቃልን በመጠቀም ያልታወቁ ቃላትን ትርጉም መወሰን።
ትርጉም ለመፍጠር የጋራ ውይይቶችን ተጠቅሞ በቀድሞ እውቀትና በአዲስ ይዘት
መካከል ግንኙነት መስራት።
ምሳሌ፡ "የመሬት ገጽታ" (landform) ምን እንደሆነ ለመተርጎም ተማሪዎች
ከመሬት ገጽታ (landform) ጋር የተዛመዱ የቃላት ዝርዝር ሊሰሩ የሚችሉ ሲሆን
በዚህ መልክም "አቧራ፣ ምድር፣ ሳር፣ ተራራዎች፣ ወለል፣ መሬት፣

ውሃ"(dirt,land,grass, mountains,the ground, earth, water) ይሆናሉ።
ከውይይት በኋላ ተማሪዎች "የመሬት ገጽታዎች የምድር ክፍሎች ይመስሉናል"
ብለው መደምደሚያ ሊያደርጉ ይችላሉ።
የቃላት :ዝርዝር ዝግጅት:
ልጅዎ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ቃላትን እንዲፈጥር ይገፋፉ።
ለምሳሌ፣ በ"መጥፎ" (bad) ምትክ "አስፈሪ" (horrible) ወይም "ጥሩ ያልሆነ " (poor)
መጠቀም።
በንባብ ወቅት ስር ቃላትን መለየት። የሙሉ ቃሉን ትርጉም ለመወሰን የታወቀን ስር መጠቀም።
የቅድመ-ቅጥያ አና ስር ቃል ምሳሌ፡ መቅደም
ቅድመ-ቅጥያ
ስር ቃል
ቅድመ=በፊት
እይታ= መመልከት ወይም ማስተዋል
መቅደም= በፊት ማስተዋል ወይም መመልከት
ዋና ሃሳብ፡ በመረጃዊ ጽሁፍ ውስጥ፣ አንባቢ እንዲያውቀው ደራሲው/ዋ የሚፈልገው ማዕከላዊ ነጥብ
የጽሁፍ መለያዎች: አንባቢ መረጃ ለማግኘትና ለመረዳት የሚያግዙ የጽሁፍ አካላት፣ ለምሳሌ፡ ርዕሰ አንቀጽ፣ የይዘት ማውጫ፣ የቃላት ዝርዝር፣ ኤሌክትሮኒክ ማውጫ/መግለጫ፣ ወካይ
ምስል/ምልክት፣ ደማቅ ህትመት፣ መግለጫ፣ ፎቶግራፎች፣ ርእስ ወይም አጭር ማብራሪያ ወዘተ. በጽሁፍ ውስጥ
በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ
ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs
Fly UP