...

የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች MT

by user

on
Category: Documents
19

views

Report

Comments

Transcript

የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች MT
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና
ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2
Learning Goals by Measurement Topic (MT)
በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች
MT
ተማሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ...
ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር
መረጂያዊ ፅሁፍ
ስነ ፅሁፍ


በመጠየቅና ጥያቄዎችን በመመለስ ቁልፍ ዝርዝሮችን መለየት እናም ተመሳሳይ የሆነ አንድ ታሪክን ሁለት አተረጓጎሞች
ማወዳደር።
ከተለያዩ ባህሎች ተረቶችን ጨምሮ ታሪኮችን መልሶ መንገር።

በመጠየቅና ጥያቄዎችን በመመለስ ቁልፍ ዝርዝሮችን በጽሁፍ ውስጥ መለየት።

ስለ አንድ ፅሁፍ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት በተለያዩ የፅሁፍ ገፅታዎች መጠቀም።

የደራሲውን አመለካከት መለየት።
ማየት ማለት መመልከት
እና መድገም ማለት እንደገና
ስለሆነ በድጋሚ ማየት
ማለት እንደገና
መመልከት!



ቃላትና ሃረጋትን መረዳትን ለማብራራት የታተሙ ወይም ዲጂታል መገልገያዎችን ማሰስ።
አዲስ ግንዛቤ ለማግኘት በጋራ ውይይቶች የመሳተፍ ዘዴን መጠቀም።
የአዳዲስ ቃላትን ትርጉም ለመስጠት የታወቁ የቃላት ስሮችንና የታወቁ ቅድመ
ቅጥያዎችን መጠቀም።
ምሳሌ:
ያልታወቀ ቃል-በድጋሚ ማየት
ቅድመ ቅጥያ-በድጋሚ__
ስር-ማየት
Thinking and Academic Success Skills (TASS)
አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች
ስለእውቀት ማወቅ
ትንተና
ይህም...
አንድን ሙሉ ነገር
ወድያውኑ ግልፅ ሊሆኑ
ወደማይችሉ ክፍሎች
መከፋፈል እና የሙሉውን
ነገር መዋቅር ለመገንዘብ
እንዲቻል ክፍሎቹን
ማገናዘብ።
በማንበብ፣ ተማሪዎች ...



ስለራስ አስተሳሰብ ማወቅና 
መገንዘብ እናም የራስን
አስተሳሰብ የመቆጣጠርና
የመገምገም ችሎታ መኖር። 
የተመሳሳይ ታሪክን አተረጓጎሞች
ከተለያዩ ባህሎች አንጻር ማወዳደር።
ደራሲው ለሚለው አንድ የተለየ ጉዳይ
እንዴት ምክንያትን መግለጽ ድጋፍ
እንደሚሆን መለየት።
በገጸ-ባህርያት ድርጊቶች ያሉ ቅጦችን
መፈለግ።
ያልተለመዱ ቃላትና ሃረጋትን ትርጉም ለማብራራት ከዚህ በፊት የተገኘን ዕውቀትና
ስልቶች መጠቀም።
በንባብ ወቅት መረጃ ለማግኘት እንዲረዳ አስተሳሰብን መቆጣጠር።
በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ
ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና
ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2
Learning Experiences by Measurement Topic (MT)
በመለኪያዊ ርእስ የመማር ተሞክሮዎች
ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ...
MT
ስነ ፅሁፍ



ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር
መረጂያዊ ፅሁፍ

አንድን ጽሁፍ መረዳትን ለማወቅ የአተረጓጎም ጥያቄዎችን መጠየቅ።
ሊነሳ የሚችል ጥያቄ፡ ለምንድን ነው ገጸ-ባህሪው ________ ያደረገው?
የአንድ ተረትን እንደገና መነገር ማዳመጥና ቁልፍ ዝርዝሮችን ከመጀመሪያ፣
መሃከልና መጨረሻ መናገር።
የተመሳሳይ ተረቶችን የተለያዩ አተረጓጎሞች ማወዳደር።

ቁልፍ መረጃ ወይም እውነታን በቅልጥፍና ለማመልከት የተለያዩ የጽሁፍ
ባህርያትን መጠቀም።

ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች፡
ደራሲው ይህን የጽሁፍ ክፍል ያካተተበት አላማ ምንድን ነው?
እንዴት የጽሁፉ ክፍሎች አንተ ጽሁፉ የበለጠ እንዲገባህ ረዱህ?

ደራሲው ያነሳቸውን ጉዳዮችና ደጋፊ ምክንያቶችን መለየት።

ያልታወቁ ቃላት ትርጉምን ለማብራራት የከዚህ በፊት እውቀትን እና የቃላት
መፍቻን ወይም የጀማሪ መዝገበ ቃላትን መጠቀም።
ያልተለመደ ቃልን በጥልቀት ለመረዳት መጠየቅና የተናጋሪን ጥያቄዎች
መመለስ።
ያልታወቁ ቃላትን ትርጉም ለመወሰን መነሻ/ስር ቃላትን ማመልክትና
መጠቀም።


በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ...





ሁልቀን አንብቡ። አቀላቅሉት! ትረካዎችን፣ መረጃዊ ፅሁፎች፣ የምግብ ባልትናዎች፣ መፅሄቶች፣
ዲጂታዊ መገልገያዎች፣ ወዘተርፈ ማንበብ።
የገጸ-ባህርያትን የአመለካከት ልዩነት ዕውቅና ለመስጠት የተለያዩ ድምጾችን በመጠቀም ለቤተሰብ
አባል አንድን ታሪክ ማንበብ ወይም በድርጊት ማሳየት።
የአንድ ተረትን ሁለት አተረጓጎሞች በቴፕ፣ ሲዲ ወይም ድረ-ገጽ መስማትና ማወዳደር።
በመጽሄቶች፣ ጋዜጣዎች እና በኮምፒወተር የሚገኙ መጣጥፎችን
መፈለግ
የጽሁፍ ባህርያትን/ገጽታዎችን ለማመልከትና ለመሰየም።
የአንድ ጽህፍን ዋና ርእስ ለመለየት የቁልፍ ቃላት ወይም ሃረጋት ዝርዝር ማዘጋጀት።
ምሳሌ፡ ከበረሃ መጣጥፍ ቁልፍ ቃላት
ሙቀት፣ ደረቅ፣ አሸዋማ፣ በማታ ብርዳማ፣ ፀሀያማ፣ ጥቂት እፅዋት፣ በቀን
የሚተኙና ሌሊት የሚወጡ እንስሳት
ዋና ርእስ = የበረሃ ባህርያት/ገጽታዎች

ከተረቶች የሚገኙ ቃላትን በመጠቀም የአተረጓጎም ጥያቄዎችን መጠየቅና መመለስ መለማመድ።
ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች፡
ይበልጥ የወደድከው የተረቱ ክፍል የትኛው ነው እና ለምን?
መቼቱ ቢለወጥ እንዴት በታሪኩ ተፅእኖ ሊያደርስ ይችላል?
የቃላት
ትርጉም
ዝርዝር/
አጭር
መዝገበ
ቃላት
ቁልፍ ዝርዝሮች፡ በጽሁፍ ውስጥ ያለን መልዕክት ወይም ርእስ የሚያጠናክሩ ዝርዝሮች
በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ
ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs
Fly UP