Comments
Transcript
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 4፣ ክፍል 2 የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት (Learning Goals by Measurement Topic - MT) MT ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር መረጂያዊ ፅሁፍ ተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት ... በታሪካዊ ክውነቶች እና በየህይወት ታሪክ መካከል ያለውን ግንኙነት ማግለፅ። በፅሁፍ ውስጥ ቁልፍ ዝርዝሮችን ለመወሰን ጥያቄዎች ማቅረብና መልስ መጠት። መረጃን ለመጠቆምና በፅሁፍ ውስጥ የቃላትንና የሀረጎችን ትርጉም ለማብራራት በፅሁፍ ገፅታዎች መገልገል። በአንድ ርእስ በቀረቡ ሁለት ፅሁፎች ዋና ዋና ነጥቦችን ማወዳደር። የአንድ ፅሁፍ ክፍል ዋናውን ርእስ ለመለየት በቁልፍ ዝርዝሮች መገልገል። ያልታወቁ ቃላትን ትርጉም ለማብራራት በአጭር የቃላትና የሀረጎች መግለጫ እና በመዝገበ ቃላት መገልገል። በከፍተኛ ድምፅ ከተነበቡ የህይወት ታሪኮች ቁልፍ ዝርዝሮችን መልሶ መንገር። አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች (Thinking and Academic Success Skills -TASS) ጥረት/ብርታት/ተነሳሽነት ገንቢ ትንተና ይህም... በማንበብ፣ ተማሪዎች... የአንድ ጠቅላላ ጽንሰ ሃሳብ መረዳትን ለማዳበር ወይም አዲስ ወይም ብቸኛ ሙሉ ለመፍጠር የተለያዩ ከፍሎችን አንድ ላይ ማገጣጠም። አንድን ግብ ለመምታት ወይም ፕሮብሌም ለመፍታት በብርታት መስራትና በውጤታማ ስልቶች መጠቀም፤ እንቅፋቶች ፊት ለፊት ወይም ተወዳዳሪ ተፅእኖዎች ቢኖሩም መቀጠል። ስለ አንድ ታሪካዊ ግለሰብ አጠቃላይ ድምዳሜ ለማድረግ በቀደምት እውቀትና በአዳዲስ መረጃዎች መገልገል። በአንድ ታሪካዊ ሰው ህይወት ውስጥ የክውነቶችን ቅደምተከተል ለመገንዘብ የሚያስችል ቀላል በሆነ መንገድ መረጃዎች ለማሳየት ስእላዊ ማደራጃዎች መፍጠር። በክንውኖች ተመሳሳይነቶችና ልዩነቶችን ለመለየት ሀሳቦችን ማደራጀትና ማገጣጠም። የማይታወቁ ቃላትን ትርጉሞች ለመወሰን በውጤታማ ስልቶች ለመጠቀም የሙጥኝ ማለት። ገና ተከናዋኝን መለየት ግቦችን መፈታተን፣ የ"እችላለሁ" አቋም እያሳዩ። የግብ ውጤትን እና ታሪካዊ ሰዎችን እንዴት ለክንውን እንደሚያነሳሳቸው መግለፅ። "እንደምችል አውቃለሁ" "ይህ አስፈላጊ ነው" "እኔ ነኝ" "አደርገዋለሁ" "አስተካክላለሁ" በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 4፣ ክፍል 2 የመማር ተሞክሮዎች በመለኪያ አርእስቶች (Learning Experiences by Measurement Topic - MT) ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር መረጅያዊ ፅሁፍ አጭር መዝገበ ቃላት የጊዜ መስመር በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ... ናሙና ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... MT የህይወት ታሪኮች ማንበብ። በአንድ ሰው ህይወት ስላለፉት አስፈላጊ ክውነቶች ጥያቄዎች ማቅረብና መመለስ እናም እነዚያ ክውንውኖች በታሪክ ላይ ምን ተፅእኖ እንዳደረጉ መግለፅ። ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች፡_____ መቼ ተወለደ/ች? የ_____ የሥራ ውጤቶች አለምን እንዴት የተሻለች ቦታ እንድትሆን አስቻሉ? የጊዜ መስመርን የመሳሰሉ፣ እንደ የፅሁፍ መዋቅር (ቅደምተከተል) እና የፅሁፍ ገፅታዎች፣ በአንድ ሰው ህይወት አስፈላጊ ክውነቶች መካከል እንዴት ግንኙነቶች እንዳሉ እንደሚያሳዩ መወሰን። ስለ አንድ ሰው የቀረቡ ሁለት የህይወት ታሪኮች እጅግ በጣም አስፈላጊ ነጥቦችን ማወዳደር። የማይታወቁ ቃላትን ትርጉም ለማብራራት በተቀዳሚ እውቀት እና በህትመት ወይም በዲጂታል መዝገበ ቃላት መገልገል። መረጃን መልሶ ለመተረክ እና በጠራ ሁኔታ ለማገናኘት በአዳዲስ የቃላት ዝርዝር መገልገል። ሁልጊዜ ማታ ማንበብ። ከአንድ የቤተስብ አባል ጋር ቃለ መጠየቅ ማድረግ እና የህይወቱ/ቷ ተቀዳሚ ክውነቶችና ፍፃሜዎች የመስመር ጊዜ መፍጠር። እሱ/ሷ ስለሚያሞግሰው/የምታሞግሰው ሰው (ስፖርተኛ፣ ዘፋኝ፣ አርቲስት፣ ወዘተ.) ማንበብ እናም በግለሰቡ አስፈላጊ ፍፃሜዎች ላይ መወያየት። ሊቀርቡ የሚችሉ ጥያቄዎች፡አንድን ግብ ለማግኘት _____ እንዴት አድርጎ ነው ጥረትና ትጋት ያሳየው። አንድን ፈተና ለመወጣት መቼ ነው ትጋት ያሳየኸው/ሽው? የአንድ ታሪካዊ ግለሰብ ሚና መውሰድ/መከተል። በአለባበስና የግለሰቡ/ቧን ህይወት አስፈላጊ ክውነቶች መልሶ በመተረክ ገፀባህሪዩን መምሰል። ቀፅል/ቀፅይ፡- የWashington, D.C.ን ታሪካዊ ግለሰቦች ሀውልቶች መጎብኘት (በተዘዋዋሪ ወይም በአካል)። http://www.nps.gov/nacc/index.htm biography (የህይወት ታሪክ)፡- በሌላ ሰው የተፃፈ የአንድ ግለሰብ የህይወት ታሪክ ቁልፍ ዝርዝሮች፡ በጽሁፍ ውስጥ ያለን መልዕክት ወይም ርእስ የሚያጠናክሩ ዝርዝሮች main topic (ዋና ርእስ)፡- የአንድ መረጂያዊ ፅሁፍ አርእስት text features (የፅሁፍ ገፅታዎች)፡- እንደ አርእስት፣ ማውጫ፣ አጭር መፍትሄ ቃላት፣ ኤሌክትሮኒክ ሜኑዎች፣ አዶዎች፣ ድርብ ፊደል፣ መለያዎች፣ ፎቶግራፎች፣ መግለጫዎች፣ ወዘተርፈ የመሳሰሉ አንባቢ መረጃዎችን ፈልጎ እንዲገነዘብ የሚያግዙ የፅሁፍ ክፍሎች በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs