Comments
Transcript
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተዜና Measurement Topic MT 2
የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተዜና ማርክ ምስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 1 በMeasurement Topic (በመለኪያ አርእስት) (MT) የመማር ግቦች MT ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር ስነ ፅሁፍ መረጂያዊ ፅሁፍ ተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት ... አንድን ፅሁፍ ለመፃፍ የደራሲን አላማ ማወቅ። ስለ አንድ ፅሁፍ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት በተለያዩ የፅሁፍ ገፅታዎች መጠቀም። አንድን ፅሁፍ ይበልጥ ለመገንዘብስእሎች፣ ፎቶግራፎች፣ እና ንድፎች እንዴት እንደሚያግዙ ማብራራት። በተረት ውስጥ በፕሎት/ዋና ክዋኔ እና በማእከላዊ መልእክት መካከል ያለውን ግንኙነት መተንተን። የተቀራረበ ትርጉም ያላቸው ቅፅሎችን መለየት። የታወቁ ስር/መነሻ ቃላት (root words) እና የታወቁ ቅድመ-ቃላት (prefixes) በመጠቀም የአዳዲስ ቃላትን (እንደ፡ “un” ማለት አይደለም እና “equal” ማለት ያው/እኩል፣ ስለዚህ “unequal” ማለት ደግሞ ያው ያልሆነ) ትርጉም መለየት። ያልተለመዱ ቃላት ወይም ሀረጎች ትርጉሞች ለማብራራት የአገባብ ቁልፎችና መዝገበ ቃላት መጠቀም። Thinking and Academic Success Skills (TASS) (አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች) ስለእውቀት ማወቅ ትንተና ... ነው በማንበብ፣ ተማሪዎች ... አንድን ሙሉ ነገር ወድያውኑ ግልፅ ለማይሆኑ ክፍሎች መበተን እና የሙሉውን መዋቅር ለመገንዘብ ክፍሎቹን መመርመር። ታሪኮችንና መረጃዊ ፅሁፍን ለመገንዘብ ከማንበብ በፊት፣ በንባብ ግዜ፣ እና በኋላ ጥያቄዎች ማቅረብ። ያልተለመዱ ቃላትን ትርጉም ለማብራራትና ለመወሰን በቀዳሚ እውቀት መጠቀም። መረጃዊ ፅሁፍ ይበልጥ ለመገንዘብ የፅሁፍ ገፅታዎችን እንዴት እንደምትጠቀም ማሰብ ማወቅና ስለ ግላዊ አስተሳሰብ ንቁ መሆን እንዲሁም የራስን አስተሳሰብ ለመቆጣጠርና ለመገምገም ችሎታ መኖር። ትረካዎችንና መረጃዊ ፅሁፎችን ለመገንዘብ ጥያቄዎችን አስቀድሞ፣ በዚያኑ ወቅት፣ እና ከማንበብ በኋላ ማቅረብ። ያልተለመዱ ቃላትን ትርጉም ለመወሰንና ለማብራራት በቀዳሚ እውቀት መጠቀም። መረጃዊ ፅሁፍ ይበልጥ ለመገንዘብ የፅሁፍ ገፅታዎች እንዴት እንደመትጠቀም ማሰብ። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የሁለተኛ ክፍል የንባብ መልእክተዜና ማርክ ምስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 1 በMeasurement Topic (መለኪያዊ ርእስ) (MT)የመማር ተሞክሮዎች ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... መረጅያዊ ፅሁፍ MT ስነፅሁፍ በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ... በፅሁፍ ውስጥ ቁልፍ ዝርዝሮችን ለመለየት ጥያቄዎችን ማቅረብና መመለስ። የፅሁፍ ገፅታዎች፣ እንደ ፎቶግራፎች፣ ካርታዎች፣ እና ንድፎች፣ ስለ አንድ ርእስ ተጨማሪ መረጃ እንደሚሰጡና ግንዛቤም ለመገንባት እንደሚያግዙ ግለጽ። ለምሳሌ፣- የበረሃ ስእል ስለ አየር ጠባዩ ዝርዝሮች ይሰጣል። አንድንድ ፅሁፍ ለመፃፍ በገፋፋው የደራሲ አላማ መወያየት። ሊቀርብ የሚችል ጥያቄ፡- ደራሲው ፅሁፉን የፃፈው አንድ ርእስ ለማብራራት ነው ወይስ አንድን ተግባር እንዴት እንደሚከናወን ለማስተማር? አንድ የፅሁፍ ባህርይ ለፈተናዎች እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ እና ከተሞክሮው እንዴት እንደሚማር መግለፅ። በኣንድ የአበው ተረት ማእከላዊ መልእክት መወያየት። ሊቀርብ የሚችል ጥያቄ፡- በባህርያት፣ አቀማመጥ፣ የታሪክ ቅደም መከተል፣ እና በመዋቅር መካከል ያለ ግንኙነት ማገናዘብ እንዴት አድርጎ ስለታሪኩ የናንተን ግንዛቤ ጥልቀት ይሰጠዋል? ሁልቀን አንብቡ። አቀላቅሉት! ትረካዎችን፣ መረጃዊ ፅሁፎች፣ የምግብ ባልትናዎች፣ መፅሄቶች፣ ዲጂታዊ መገልገያዎች፣ ወዘተርፈ ማንበብ። አንድ አርእስት ምረጡ እና እንደ ማውጫ፣ ጥቅስ ያላቸው ስእሎች፣ ንድፎች፣ ወዘተርፈ የመሳሰሉ ገፅታዎች ያሉት መፅሃፍ ማፍራት። የምግብ ባልትና ፅሁፍ፣ የግጥሚያ መግለጫዎች፣ እና የንግድ ማስታወቂያዎች አንብቡና እነሱን ያስፃፈው የደራሲን አላማ መግለፅ። ከማንበብ በፊት ስለ አንድ አርእስት ጥያቄዎች ማዘጋጀት እናም በማንበብ ግዜ መልሶች ማግኘት። ትምህርት ያለው የአበው ተረት ንገሩ፣ ፃመፃፍ፣ ወይም መሳል። የተወስኑ ባህርያትን የአበው ተረቶች ጠባዮች ባህርያት፡_ ሰብአዊ፡ የእንስሳ፣ ወይም መለኰታዊ አካላት ለማግኘት የተለመደ አቀማመጥ/አካባቢ፡- ባህል ወይም ወቅት ያንፀባርቃል የአበው ተረት ፕሮብሌም፡- ክውነት ወይም ሁኔታ የሚፈጠር፣ አብዝኛውን በ ከቤተመፃህፍት በባህርይ ድክመቶች ማንበብ። መፍትሄ፡- ፕሮብሌሞች የሚፈቱት ብዙውን ግዜ በአንድ ባህርይ የበሰለ ምላሽ፤ መዝገበ ቃላት ቋንቋ፡ የቃላት ዝርዝር ጉዞ ወይም ምትሀት ሊያካትት ይችላል ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ቅፅሎች መዘርዘር (ትልቅ፣ ግዙፍ፣ ወዘተርፈ) ከመፅሄቶች፣ የቀን መቁጠርያዎች፣ እና የንግድ ካታሎጎች ስእሎችን ተመልከቱ ወይም ቆርጣችሁ አውጡ እና ስእሎችን ለመግለፅ የተቻላችሁን ያህል ብዙ ቅጽሎች አድርጋችሁ ስእሎቹን ግመግለፅ። የሚቻሉ መልሶች፡- ግራጫ፣ የተዥጐረጐረ፣ ፈጣን፣ ለስላሳ፣ ፀጥ ያለ መእከላዊ መልእክት፡- ደራሲው/ዋ በታሪኩ/ኳ ማስተላለፍ የሚፈልገው/የምትፈልገው ትምህርት ወይም መልእክት የታሪክ ቅደም ተከተል፡- ታሪክን የሚገነቡ የክውነቶች ፣ ፕሮብሌሞች፣ እና መፍትሄዎች የተደራጀ ቅርፀት ወይም ቅደም ተከተል በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs