Comments
Description
Transcript
የሁለተኛ ክፍል የሂሳብ ትምሀርት መልእክተ ዜና MT
የሁለተኛ ክፍል የሂሳብ ትምሀርት መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2 Learning Goals by Measurement Topic (MT) በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች MT መጠንና የመጠን መረጃዎች/ አሀዞች ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች ተማሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ... ባለ 2 መደብ ቁጥሮች አስር ቁጥር አጠናቅረው ወይም ሳያጠናቅሩ (አስር አንዶችን አጋጥሞ) የመደመር ስልት መጠቀም። ባለ 2 መደብ ቁጥሮች ለመቀነስ አስር ቁጥር በትነው ወይም ሳይበትኑ ስልት መጠቀም (አንድ አስርን ወደ አንዶች መሰባበር)። አንድን ፕሮብሌም ለመፍታት አንድን የመደመር ወይም የመቀነስ ስልት እንዴት እንደተጠቀሙ ለማሳየት የጽሁፍ ዘዴን መጠቀም። የአንድ ስብስብ ሳንቲሞችን ዋጋ ለመወሰን መቁጠርን መዝለል። ሁሉንም ባለ1 መደብ ቁጥሮች በቅልጥፍና (በትክክል፣ በብቃትና በበርካታ መንገዶች) ለመደመርና ለመቀነስ ስልቶችን መጠቀም። ክባለ 2 መደብ ቁጥሮች ጋር የተያያዙ የቃል ፕሮብሌሞች ለመፍታት የመደመርና የመቀነስ ስልቶች ተጠቀሙ። ከ1-100 የቁጥር መስመር ላይ በቁጥሮች መካከል እኩል ቦታ እርቀት እንዲኖር አድርጎ ሙሉ ቁጥሮችን መወከል። አንድ የቁጥር መስመር በመጠቀም ድምሮችንና ልዪነቶችን መሰየም። ድምር 12 + 23 = 35 ልዩነት 57 – 13 = 44 ሳንቲሞችና የወረቀት ገንዘቦች በመጠቀም የቃላት ፕሮብሌሞችን መፍታት። Thinking and Academic Success Skills (TASS) አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች ስለእውቀት ማወቅ ትንተና ይህም... በሂሳብ ትምህርት፣ ተማሪዎች ... አንድን ሙሉ ነገር ወድያውኑ ግልፅ ሊሆኑ ወደማይችሉ ክፍሎች መከፋፈል እና የሙሉው ቁጥር መዋቅር ለመገንዘብ እንዲቻል ክፍሎቹን ማገናዘብ። ቁጥሮችን በመገንባትና በመሰባበር ስልቶች መካከል ያሉ ተመሳሳይነቶችና ልዩነቶችን ማብራራት። ፕሮብሌምችን ለመፍታት በመደመር ወይም በመቀነስ ሁኔታ የታወቁና ያልታወቁ ክፍሎችን መለየት። የግል አስተሳሰብን ማወቅና በህላዌነቱ መንቃት እንዲሁም የራስን አስተሳሰብ መቆጣጣርና መገምገም መቻል። ከዚህ በፊት የሚታወቅን የቁጥር ቦታን ዋጋ በመጠቀም ተገቢ መገልገያዎችን (የቁጥር መስመር፣ መቁጠሪያ፣ ባለ አስር ቁጥሮች ማዕዘን፣ ኪዩቦች ወዘተ) በመምረጥ አንድን ፕሮብሌም መፍታት። ባለ 2 መደብ ቁጥሮችን በመደመርና በመቀነስ ወቅት የቁጥሮች ዋጋ ቦታ ግንኙነቶች ትክክለኛነትን ለማረጋገጥና ስህተቶችን ለማረም እንዴት እንደሚጠቅሙ ማብራራት። የስብስብን ዋጋ ለመወሰን ሳንቲሞችን ስለመመደቢያ ዘዴ ማሰብ። ፕሮብሌም ሲፈታ ስህተቶችን ለማረም ራሳችሁን ተቆጣጠሩ። 57 - = 45 የሳንቲም ባህርያትን (መጠን፣ ቀለም፣ ምስል፣ ዋጋ፣ ሽካራነት) ተመሳሳይና ልዩነት ማወዳደር። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የሁለተኛ ክፍል የሂሳብ ትምሀርት መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2 Learning Experiences by Measurement Topic (MT) በመለኪያዊ ርእስ የመማር ተሞክሮዎች ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... MT በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ... 36 - 18 = በርካታ ያልታወቁ ቦታዎችን የያዙ ቀመሮችን መጻፍና መፍታት። የቦታን ዋጋ መሰረት ያደረጉ ስልቶችን (ሞዴል በመሳል፣ የቀጥር መስመር በመፍጠር፣ ቁጥሮችን በመከፋፈል፣ ወዘተ) በመጠቀም መደመርና መቀነስ። የቃላት ፕሮብሊሞችን መፍታት ማወዳደር። ባለሁለት ደረጃ የቃላት ፕሮብሌምችን ከቀመሮች ጋር ማጣመርና መፍታት (በአውቶብስ ውስጥ 23 ተማሪዎች አሉ። በመጀመሪያው መቆሚያ 5 መጠንና የመጠን መረጃዎች/አሀዞች በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች ባለ 2 መደብ ቁጥሮችን ለመቀነስ ቀመር መጻፍ። ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ 36 - = 18 - 18 = 18 18 = - 18 ምሳሌ፡ ሬድስኪንስ 35 ነጥቦች አገኘ። ጂያንትስ 24 ነጥቦች አገኘ። የውጤቶች ድምር ስንት ነው? 35 + 24 = 59 ነጥቦች ሬድስኪንስ ከጂያንትስ ስንት የሚበልጡ ነጥቦች አገኘ? 35-24 = 11 ተጨማሪ ነጥቦች በቤት ውስጥ የተገኙ ልምዶችን በመጠቀም በሁሉም ቦታዎች ያልታወቁ የሚያካትቱ የቃላት ፕሮብሌሞችን መፍጠር። በቤት ውስጥ የተገኙ ልምዶችን በመጠቀም የቃላት ፕሮብሌምችን መፍጠርና ማወዳደር። ተማሪዎች ወረዱ። በሁለተኛው መቆሚያ 3 ተጨማሪ ተማሪዎች ተሳፈሩ። አሁን በአውቶብስ ውስጥ ስንት ተማሪዎች አሉ?)። መማር የሚደግፉ ድር ጣብያዎች፡- http://www.mathplayground.com/TB_AS/tb_as3_iFrame.html - http://www.mathplayground.com/TB_AS/tb_as5_iFrame.html የተሰበሰቡ ሳንቲሞችን ዋጋ ለመወሰን (የዶላር ግማሽ፣ ሃያ አምስት ሳንቲም፣ አስር ሳንቲም፣ አምስት ሳንቲም፣ አንድ ሳንቲም) መቁጠርን መዝለል። አንድ ዶላር የሚሆኑ ሳንቲሞች ስብስብ መፍጠር። = 50¢ + 25¢ + 10¢ + 10¢ + 5¢ = $1.00 ስዕሎች ለመመዘኛነት ያልተሳሉ ዳይስ፣ ማሽከርከሪያዎች ወይም ካርዶችን በመጠቀም ባለ 2 መደብ ቁጥሮችን መስራት። የመደመር ወይም የመቀነስ ቀመር መጻፍና መፍታት። የቤት ዕቃዎችን በመሰብሰብ የመደመርና የመቀነስ ቀመሮችን (13 አሻንጉሊት መኪናዎች + 12 አሻንጉሊት የጭነት መኪናዎች = ስንት ተሽከርካሪዎች ናቸው?) መፍጠርና መወከል የስፖርት ውጤቶችን በጋዜጣ ወይም በኮምፒውተር መመልከት። የተገኙ ውጤቶችን ድምር ለመናገር ቀመር መጻፍ ወይም በሁለት ውጤቶች መካከል ያለን ልዩነት ለመናገር ቀመር መጻፍ። አስከ $5 የሆነ ዋጋ ለመወሰን የሚያስችሉ የሳንቲሞችና የወረቀት ገንዘብ ስብስብ ማደራጀትና መቁጠር። የተለያዩ ሳንቲሞችን መለየትና መቁጠር መለማመድ። ከተለያዩ ስቴቶች ኳርተሮችን (ሃያ አምስት ሳንቲሞች) መሰብሰብና በእያንዳንዱ ኳርተር ያለን ልዩነት መተንተን። ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች፡ የእያንዳንዱ ሳንቲም ዋጋ ምን ያህል ነው? በእያንዳንዱ ሳንቲም የሚታዩ ምስሎች ምንድን ናቸው? ተመሳሳይ መጠን ያላቸው የተቀላቀሉ የወረቀት ገንዘብና ሳንቲሞች መቁጠርን መለማመድ። ስብስቦች ለምን እኩል እንደሆኑ ማብራራት። መማርን ለማገዝ የሚረዳ ድረ ገጽ፡ - http://www.usmint.gov/ በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs