የአራተኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርት መልእክተ ዜና በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች MT
by user
Comments
Transcript
የአራተኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርት መልእክተ ዜና በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች MT
የአራተኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርት መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2 በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች Learning Goals by Measurement Topic (MT) MT አለካክና አሀዞች በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች ተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት፡ አንድን ሙሉ ቁጥር (እስከ አራት ቦታ/ዲጂት ያለው) በባለ አንድ ቦታ/ዲጂት አካፋይ ቁጥር (1) ማካፈል። በማካፈል ፕሮብሌም የቀሪን ትርጉም ማስረዳት። ቀመሮች፣ ባለአራት ማእዘን ሰልፎች፣ እና ወይም የስፋት ሞዴሎች በመጠቀም የማካፈልን ስሌት መሳልና ማብራራት። ርቀት፣ ግዜ፣ ግዝፈት፣ እና ገንዘብ የሚያካትቱ የቃል ፕሮብሌሞችን ለመፍታት በመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛት፣ እና ማካፈል መጠቀም። የባለ አራት ማእዘን የስፋትና የመጠን ዙርያ ፎርሙላዎች በመጠቀም የተጭባጩን አለም ፕሮብሌሞች መፍታት። ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ መደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛት፣ እና ማካፈል የሚያካትቱ ባለበርካታ ደረጃ ፕሮብሌሞች መፍታት። ቀሪ ያላቸውን ፕሮብሌሞች ጨምሮ፣ መልሶች ተቀባይነት እንዳላቸው መወሰን። ያልታወቁ ቁጥሮችን በተለዋዋጮች ማመልከት። አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች Thinking and Academic Success Skills (TASS) ጥረት/ተነሳሽነት/ብርታት ማብራራት ... ነው በሂሳብ ትምህርት፣ ተማሪዎች የሚያደርጉት ... የሚያስፋፉ፣ የሚያበለፅጉ፣ ቀሪዎችንና በፕሮብሌም ውስጥ ያላቸውን ትርጉም በመጨመር የማካፈልን ትርጉም ማስፋፋት። ወይም የሚያስጌጡ ዝርዝሮች እንደመደመርና መቀነስ የመሳሰሉ የቀድሞ ትምህርት ፅንሰሃሳቦች በማስፋፋት የቃል ፕሮብሌሞች መጨመር። ማሟላት። አንድን ግብ ለመምታት ወይም ይበልጥ ውስብስብና አሳሳቢ የቃል ፕሮብሌሞችን መሞከር። አንድን ፕሮብሌም ለመፍታት በርትቶ መስራትና ውጤታማ እንቅፋቶችን ለመወጣት የሚያስችል የማካፈል ፕሮብሌሞችን ለመፍታት በርካታ ስልቶችን ማዳበር። ስልቶችን በስራ ላይ ማዋል፤ መሰናክሎችና ተፎካካሪ ጉዳዮች/ሃይሎች እየተቋቋሙ መቀጠል። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የአራተኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርት መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2 Learning Experiences by Measurement Topic (MT) በመለኪያዊ አርእስት የመማር ተሞክሮዎች MT በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ... ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች የቦታ ዋጋ፣ ሰልፎች፣ እና የስፋት ሞዴሎች በመጠቀም ሙሉ ቁጥሮችን ማካፈል። የሰልፍ ሞሞሞ የስፋት ሞደል ርቀት፣ ግዜ፣ ግዝፈት፣ እና ገንዘብ የሚያካትቱ ባለ በርካታ ደረጃ የቃል ፕሮብሌሞች መፍታት። ለምሳሌ፡- የትምህርት ቀን በ8:50 a.m. ተጀምሮ በ3:05 p.m. ያልቃል። የቀኑ ርዝመት ምን ያህል ነው? አጭር ወፍትሄ ቃላት ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ አለካክ እና አሀዞች ተለዋዋጮች የሚያካትቱ ባለ በርካታ ደረጃ የስፋትና የመጠነ ዙርያ የቃል ፕሮብሌሞች መፍታት። ለምሳሌ፡- የዚህን መናፈሻ ቦታ ስፋት ለማወቅ ስለ መጠነ ዙርያ በምታውቀው መጠቀም። የማካፈል ፕሮብሌሞች በጋርዮሽ በሚፈቱበት ወቅት የቀሪን ትርጉም ማብራራት። ከ0 – 10 ማባዛትና ማካፈል እውነታ መለማመድ። የማካፈል ፕሮብሌም መፍቻ ስልቶችን መጋራትና መለማመድ። በስልቶች መካከል ልዩነት ማብራራት። አዝራሮች፣ ሳንቲሞች፣ ብሎኮች የመሳሰሉ መሳሪያዎች በመጠቀም የማካፈል ፕሮብሌሞች ሞዴል ማድረግና መፍታታ። ቀሪ ምን እንደሆነ መወያየት። የስራ ፕሮግራም፣ የምግብ ባልትና፣ የጉዞ ርቀት፣ ወይም የጠፋ ገንዘብ የሚያካትቱ የተጭባጩ ህይወት የቃል ፕሮብሌሞች መፍጠርና መፍታት። ለምሳሌ: ዛሬ ስንት ሰአት ነቅተህ ነበር? የራት ዋጋ ስንት ነበር? እቤት አካባቢ የሚገኙ አራት ማእዝኖች (ጠረጴዛዎች፣ ምድጃ፣ ፍሪጅ፣ አልጋ፣ ወዘተርፈ) ስፋትና መጠነ ዙርያ ለማግኘት በፎርሙላዎች መጠቀም መለማመድ። መልሱ ለምን ልክ እና ሚዛናዊ መሆኑን ማስረዳት የተለመዱ የቤት እቃዎች በመጠቀም የቃል ፕሮብሌሞችን መፍጠርና መፍታት። መልሶቹ ለምን ልክና ሚዛናዊ እንደሆኑ ማብራራት። ማካፈያ፡- ሌላ ቁጥር የሚካፈልበት ቁጥር። ተለዋዋጭ፡- ያልታወቀን መጠን ለመወሰን የሚያገለግል አንድ ምስል (ባብዛኛው አንድ ፊደል)። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs