...

የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT

by user

on
Category: Documents
20

views

Report

Comments

Transcript

የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT
የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት
ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2
የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት
(Learning Goals by Measurement Topic - MT)
MT
ጂዮሜትሪ
አለካክና አሀዞች
ቁጥርና ግብረቶች ክፍልፋዮች
ተማሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ...
 ክፍልፋይን በሙሉ ቁጥር ማባዛት።
 ክፍልፋይን በሙሉ ቁጥር ማባዛት የሚያካትት የቃል ፕሮብሌም መፍታት።
 በፕሮትራክተር በመጠቀም ማእዝኖችን ለክቶ መንደፍ።
 ማእዝኖችን መስራትና ማፍረስ።
 ርቀትን፣ ጊዜን፣ መጠን፣ ክብደት፣ እና ገንዘብን የሚያካትቱ የቃል ፕሮብሌሞች ለመፍታት በክፍልፋዮች መደመር፣
መቀነስ፣ እና ማባዛት መጠቀም።
 መስመሮችን፣ የመስመር ክፍሎችን፣ ማእዘናዊ (perpendicular) መስመሮች፣ እና ትይዩ (parallel) መስመሮችን
መሳልና መለየት።
 ተመሳሳይና ትይዩ መስመሮችን በባለ ሁለት ልኬት ቅርፆች (two-dimensional shapes) መስራትና መለየት።
 ማእዘኖችን፣ ዝርግ (reflex) ማእዘኖችን ጨምሮ፣ መሳልና መለየት።
 ባለሶስት ማእዘኖችን እና ሌሎች ባለ ሁለት ልኬት ቅርፆችን በማእዘን እና በመስመር ጥባይ መሰረት
መካፋፈል/መደርደር።
አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች
(Thinking and Academic Success Skills -TASS)
ጥረት/ተነሳሽነት/ብርታት
ማብራራት
MT
ይህም...
በሂሳብ ትምህርት፣ ተማሪዎች የሚያደርጉት ...
የሚያስፋፉ፣ የሚያበለፅጉ፣  አንድን ክፍልፋይ በሙሉ ቁጥር ለማባዛት አንድ ስልት መምረጥና ስለ ምርጫው ማሳመን
ወይም የሚያስጌጡ
(ደጋፊ መርጃዎች ማቅረብ)።
ዝርዝሮችን መጨመር።  የቃል ፕሮብሌሞች አፈታት ላይ የተወሰነ ስልት አጠቃቀም የተሳካበትንና ያልተሳካበትን
ሁኔታ መወሰን።
አንድን ግብ ለመምታት
 የፅንሰሀሳቦችን ጥልቅ ግንዛቤ በሚያራምዱ የተለያዩ ስልቶች በመገልገል የፈታኝ ክፍልፋዮችና
ወይም አንድን ፕሮብሌም
የጂዮሜትሪ አለካክ ፕሮብሌሞችን መፍታት።
ለመፍታት በርትቶ
መስራትና ውጤታማ
ስልቶችን በስራ ላይ ማዋል፤
መሰናክሎችና ተፎካካሪ
ጉዳዮችን/ሃይሎችን
እየተቋቋሙ መቀጠል።
በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ
ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs
የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት
ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2
የመማር ተሞክሮዎች በመለኪያዊ አርእስት (Learning Experiences by Measurement Topic - MT)
ቁጥርና ግብረቶች ክፍልፋዮች
MT
ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ...
 በሙሉ ቁጥር ማባዛትን ለማሳየት የመደመር ድግግሞሽ በመጠቀም የአሀዱ
ክፍልፋይ እውቀት( ፣
ወዘተ) መተግበር።
ምሳሌ: x 4 = + + + =
አለካክና አሀዞች
 አንድን ክፍልፋይ በሙሉ ቁጥር ማባዛትን የሚያካትቱ የቃል ፕሮብሌሞችን
ለመፍታት ጥያቄዎች ማቅረብ።
ምሳሌ፡- በቤተሰብዎ ውስጥ ሶስት ልጆች አሉ። እያንዳንዱ ልጅ የሰአት 5/6ኛ
ያነባል። በጠቅላላ ሁሉም ስንት ሰአቶች አነበቡ?
 የቃል ፕሮብሌሞች ለመፍታት አንድን ክፍልፋይ በሙሉ ቁጥር ማባዛት እና
መልሱን ማብራራት።
 የተለያዩ የማእዘን አይነቶች ለመለካት በፕሮትራክተር መጠቀም።
 የተሰጠ መለኪያ ማእዘኖች መሳል።
 ማእዘኖችን ለመገንባትና ለማፍረስ በተለያዩ መንገዶች መወያየት።
ምሳሌ፡- ባለ 90° ማእዘን የምገነባበት ብዙ መንገዶች አሉ። ተደምረው 90°
የሚሆኑ በሆኑ ሁለት ማእዘኖች መጠቀም እችላለሁ፤ እንደ 30° እና 60°፣
10° እና 80°፣ ወይም 1° እና 89°። 3 ወይም ከዚያ በላይ በመጠቀም፣
ተደምረው 90° የሚሰጡ እንዲያውም ከዚህ የበዙ ቅንጅቶች አሉ።
 አለካክና ክፍልፋዮች የሚያካትቱ የተጨባጩ አለም ፕሮብሌሞች መፍታት።
 በቅርፆች፣ ጂዮቦርዶች (እግር ያለቸው ሳንቃዎች) እና የላስቲክ ማሰርያዎች፣
ጂዮሜትሪ
ቤት ውስጥ ልጅዎ ማድረግ የሚችለው/የምትችለው...
የቅርፅት ጡቦች፣ ካርታዎች እና በሌሎች ቁሳቁሶች በመጠቀም የጂዮሜትሪ
ገፅታዎች መለየት፣ መተንተን፣ እና መፍጠር።
 በጠጣር ቁሳቁሶች ውስጥ ጂዮሜትሪያዊ ገፅታዎች መለየት።
 በቤት አካባቢ የሚገኙ ዝርግ ስእሎች/ነገሮች ማእዘኖች በፕሮትራክተር ተጠቅሞ
መለካት። የተወሰኑ ማእዘኖች መሳልና እነሱን መለካት። በማእዘኖች በመገልገል
ስእል መፍጠር።
 ክፍልፋዮችና አለካክ የሚያካትቱ የቃል ፕሮብሌም ለመፍታት ጥያቄዎች ማቅረብ።
ምሳሌ፡ የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች በቀን 4 1/4 ሰአቶች ይሰራሉ። በአምስት ቀኖች
ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ይሰራሉ?
 የማእዘኖች፣ መስመሮች፣ ባለአራት ጎኖችና የባለሶስት ጎኖች የተጨባጩን አለም
ምስሌዎች መለየት።
 "Guess My Rule" (ደንቤን ገምት) መጫወት። በዚህ ግጥምያ፣ የእለታዊ ቁሶች
ማሰባሰብና መክፋፈል እና በመስመራቸውም ወይም በማእዝናቸው ጠባይ
የሚከፋፈሉበትን ህግ መገመት። ከዚያም ሚናዎች መለዋወጥ።
በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ
ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs
Fly UP