Comments
Transcript
የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT
የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት ማርክ መስጫ ወቅት 4፣ ክፍል 1 የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት (Learning Goals by Measurement Topic - MT) MT ቁጥሮችና ግብረቶች ክፍልፋዮች በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች ተማሪዎች ማድረግ የሚችሉት፡ አንድን ባለ 4-ዲጂት ቁጥር በ 2-ዲጂት ቁጥር ለማካፈል ቀመሮችን ( የእኩል ነው ምልክት ያላቸው የቁጥር አረፍተ ነገሮች) ፣ አራት ማዕዘን አቀማመጦች (arrays) ወይም የስፋት ሞዴሎችን መጠቀም። የማካፈል ፕሮብሌሞች ለመፍታት በቦታ ዋጋ የተመሰረቱ የመገመቻ ስልቶች፣ በግብረቶች ባህርያት፣ እና በማባዛትና በማካፈል መካከል ባለው ግንኙነት መጠቀም። በአካፋዮች፣ ተካፋዮች እና ድርሻዎች መካከል ግንኙነቶችን ማስረዳት። ድርሻ ድርሻ ምሳሌዎች፡አካፋይ ተካፋይ ተካፋይ አካፋይ አራት ግብረቶችን (+፣ - ፣ x ፣ ÷ ) ያካተቱ ፕሮብሌሞችን መፍታት። የማይመሳሰሉ አካፋዮች ያሏቸው ክፍልፋዮችን ለመደመርና ለመቀነስ በተመጣጣኝ እንደ ስልት መጠቀም። የተለያዩ አካፋዮች ባላቸው ክፍልፋዮች መደመርና መቀነስን የሚያካትቱ የቃል ፕሮብሌሞችን መፍታት። ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች ለመፍጠር እና ከተለያየ አካፋይ ካላቸው ክፍልፋዮች ለመደመር የተባዥዎችን እና ብዜቶችን ግንዝቤ ተግባራዊ ማድረግ። የማይመሳሰል አካፋይ ያላቸውን ክፍልፋዮች ለመደመር በተከፋዮችና በአካፋዮች መካከል ስላለው ግንኙነት ማሰብ። አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች (Thinking and Academic Success Skills -TASS) የአስተሳሰብ ድፍረት አወሳሰድ ግትር ያለመሆን ይህም... በሂሳብ፣ ተማሪዎች የሚያደርጉት... ለአዳዲስና ለተለያዩ ሀሳቦችና ስልቶች ክፍትና ግብር መላሽ መሆንና በመካከላቸው በነፃ መመላለስ። አንድን ግብ ለመምታት አጠራጣሪን መቀበል ወይም የዘልማድ ደንብን መፈታተን። የተመጣጣኝ ክፍልፋዮች እውቀት ተመሳሳይ ያልሆነ አካፋይ ያላቸውን ክፍልፋዮች መደመርና መቀነስ እንደሚያቃልል ማወቅ። ተመሳሳይ ያልሆነ ክፍልፋዮች ያላቸው ክፍልፋዮች ለመደመርና ለመቀነስ በተለያዩ ዘዴዎች መገልገል። ለቃል ፕሮብሌሞች መፍትሄ ለማግኘት የተለያዩ ዘዴዎች ማፍለቅ። ፕሮብሌም ሲፈታ አስተሳሰብን ማስተካከል። ...ማወቅ o ስህተቶች ማስተማር ይችላሉ። o ጎበዝ ተማሪዎች እርዳታና አስተያየት ይጠይቃሉ። o መጀመርያ ላይ ሁሉንም አለማወቅ ምንም አይደለም። o ሁሉም ከፍተኛ ግኝት ማድረግ ይችላል። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የአራተኛ ክፍል አጭር የሂሳብ መፅሄት ማርክ መስጫ ወቅት 4፣ ክፍል 1 የመማር ተሞክሮዎች በመለኪያዊ አርእስት (Learning Experiences by Measurement Topic - MT) MT ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... ቤት ውስጥ ልጅዎ ማድረግ የሚችለው/የምትችለው... የበርካታ-ዲጂት ማካፈል ፕሮብሌም (4-ዲጂት ቁጥር በ 2-ዲጂት ቁጥር) ለመፍታት የስፋት ሞዴሎችና ቀመሮችን መጠቀም። ተጨማሪ አስቸጋሪ ፕሮብሌሞችን የመፍታት ችሎታዎችን ለማዳበር በአእምሮ ሂሳብ ተጠቅሞ የማባዛትና የማካፈል ፕሮብሌሞችን መፍታት መለማመድ። ምሳሌ: 4 x 8 = 32 40 x 80 = 3, 200 3,200 ÷ 40 = 80 የቁጥርን መጠን አመልካች ቦታ እውቀት በመጠቀም ድርሻን መገመት። በማባዛትና በማካፈል መካከል ያለን ግንኙነት ለማሳየት የስፋት ሞዴልን በመጠቀም 4ዲጂት በ 2-ዲጂት የማካፈል ፕሮብሌሞችን መገመትና መፍታት። በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች ምሳሌ፡ 1,786 ÷ 40 = 44 ለመፍታት በአስር-ሺ ሰንጥረዥ መገልገል ምሳሌ፡- በስቴድየም ውስጥ 3,529 መቀመጫዎች አሉ። 40 ከፍሎች አሉ። በያንዳዱ ክፍል ስንት መቀመጫዎች አሉ? 40 x 40= 1,600 የስፋት ሞዴል ስእል ለማካፈል ቀሪ 40 x 4 = 160 ቀሪ 26 ማስታወሻ፡ ይህ የአንድ ሺ እኩል ሰንጠረዥ (grid) የተወሰነ ክፍል ነው. በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs