የአምስተኛ ክፍል የተጨመቀ የሂሳብ መልእክተ ዜና የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT
by user
Comments
Transcript
የአምስተኛ ክፍል የተጨመቀ የሂሳብ መልእክተ ዜና የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT
የአምስተኛ ክፍል የተጨመቀ የሂሳብ መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 1፣ ክፍል 1 የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት (Learning Goals by Measurement Topic - MT) MT ተማሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ... በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች ቁጥሮችና ግብረቶች ክፍልፋዮች ክፍልፋዮችን በሙሉ ቁጥር ማባዛት እና ክፍልፋዮችን በክፍልፋዮች ማባዛትን የሚያካትቱ የቃል ፕሮብሌሞችን መፍታት። ከማስተካከል (ምዘና) ጋር በተያያዘ ሁኔታ የክፍልፋይና የሙሉ ቁጥር መባዛት መለየት። ክፍልፋዮችን በክፍልፋዮች ለማባዛት በሚታዩ የክፍልፋይ ሞዴሎች (ስእሎች) መጠቀም። ክፍልፋይ የጎን ርዝመት ያላቸውን የባለአራት ማእዘኖች ስፋትን የሚያካትቱ ፕሮብሌሞች መፍታት። ክፍልፋዮችን ለማባዛት ቀልጣፋ ስልቶችን መተግበርና ማብራራት። ባለ ብዙ ዲጂት/ቦታ ሙሉ ቁጥሮችን ለማባዛት ደረጃውን በጠበቀ ቀመር (algorithm) መጠቀም። አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች (Thinking and Academic Success Skills -TASS) ትብብር ግትር ያለመሆን MT MCPS ይህም... በሂሳብ፣ ተማሪዎች የሚያደርጉት... ለአዳዲስና ለተለያዩ ሀሳቦችና ስልቶች ክፍትና ምላሽ ሰጭ መሆንና በመካከላቸው በነፃ መመላለስ። ክፍልፋዮችን በማይመሳሰሉ አካፋዮች ለማባዛት በተለያዩ ዘዴዎች መገልገል። በተለያዩ የመማር ተሞክሮዎች አማካይነት የተለያዩ ማስረጃዎች ሲቀርቡ፣ ለሚቀያየሩ ሀሳቦች፣ ጥያቄዎች፣ መገልገያዎች፣ ወይም ስልቶች ራስን የማስተካከል ችሎታ ማሳየት። ክፍልፋዮችን በሙሉ ቁጥሮች ለማባዛት የግብረቶችን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ። የቡድን ግብ ለመምታት በውጤታማነትና በመከባበር መስራት። የማባዛትን ግንዛቤ ስፋትና ጥልቀት ለመስጠት በርካታ ሀሳቦችን መሻትና ማክበር። ለፕሮብሌም አፈታት የቡድን ግብ ለመድረስ የሀላፊነቶችን መጋርያ አማራጮች መለየትና መተንተን። በጥንድ ወይም በቡድን ሆኖ የአንድን ፕሮብሌም ግንዛቤ የሚያግዙ ስልቶችን በማወዳደር ተቀባይነት ባላቸው ምላሾች መወያየት። C 2.0 Summit 2014 Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የአምስተኛ ክፍል የተጨመቀ የሂሳብ መልእክተ ዜና ማርክ መስጫ ወቅት 1፣ ክፍል 1 የመማር ተሞክሮዎች በመለኪያዊ አርእስት (Learning Experiences by Measurement Topic - MT) MT ቤት ውስጥ ልጅዎ ማድረግ የሚችለው/የምትችለው... ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... የክፍልፋይና የሙሉ ቁጥር ማባዛትን እንደ ማስተካከል (መመዘን) ብሎ መተርጎም። ? ምሳሌ፡- x 18 ከሚል መግለጫ በመነሳት፣ ከ18 በላይ፣ ያነሰ፣ እና እኩል የሆነ ? ውጢት የሚሰጥ ክፍልፋይ መፃፍ። የስፋት ሞዴል በመጠቀም ክፍልፋዮችን ለማባዛት አንድን ሙሉ ወደ ክፍልፋዮች መከፋፈል። ቁጥርና ግብረቶች - ክፍልፋዮች ምሳሌ:- ስለ ክፍልፍይ ሞዴሎች መማርን ለመደገፍ፡http://www.mathplayground.com/Fraction_bars.html አንድ የስፋት ሞዴል በመጠቀም ክፍልፋዮች ለማባዛት በተጨባጭ አለም ምሳሌዎች መጠቀም። ምሳሌ፡- የብስኩት መስርያ መመርያ ስኒ ዱቄት ይጠይቃል። የአንድ ሂደት ኛ እየሰራህ ነው። ምን ያህል ዱቄት ያስፈልግሃል? (ሌሎች መለኪያዎች ወይም የምግብ አሰራሮች በመጠቀም ተመሳሳይ ፕሮብሌሞች መሞከር።) ማሳሰብያ፡-ይህ ያንድ ሙሉው ወደ ሶስት እኩል ክፍሎች ይቆራረጣል። ከሶስቱ ክፍሎች ሁለቱ ለማሳየት ጥላት ይደረግባቸዋል ። ከዚያም ሙሉው ወደ አራት እከል ክፍሎች ይቆራረጣል። ከአራቱ ክፍሎች ሶስቱ ለመታየት ይጠላሉ (ጥላት ይደረግባቸዋል) ። አንድን ሙሉ ቁጥር በአንድ ክፍልፋይ ማባዛትና አግባብ ያለው ትግባሬ ማግኘት። ምሳሌ፡- በቀን ሰአት ብታነብ፣ ሳምንቱ ሲያልቅ ምን ያህል ሰአቶች አንብበሀል? የማስተካከል እርምጃ ምሳሌ ነው ምሳሌ፡- የቤት ስራህን የአንድ ሰአት 11/4 ኛ ሰርተሀል። በምንባብ ያሳለፍከው ነው። ለምን ያህል የሰአት ክፍልፋይ አነበብክ? የተጨባጩን አለም ፕሮብሌሞች በመፍጠር ተጣጣፊነት (ግትር አለመሆንን) ማሳየት ክፍልፋዮችን ማባዛት ትምህርት ለመደገፍ ድርጣብያ፡http://www.learner.org/courses/learningmath/number/session9/part _a/try.html ውጤቱ የተደራረበው አካባቢ ነው። x = በአስርቤት ቁጥርና ግብረቶች መልሱ MCPS ጊዜ ባለ በርካታ ዲጂት ሙሉ ቁጥሮችን ለማባዛት ደረጃውን የጠበቀ የስሌት ዘዴ መጠቀም። ለምሳሌ: ደረጃውን የጠበቀ የስሌት ዘዴ በመጠቀም በባለ በርካታ ዲጂት ሙሉ ቁጥሮች ለመለማመድ የማባዛት ፕሮብሌም ለመፍጠር ጋዜጦችና መፅሄቶች ውስጥ ቁጥሮች መፈለግ። C 2.0 Summit 2014 Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs