Comments
Transcript
የአንደኛ ክፍል ሂሳብ መጽሄት በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች MT
የአንደኛ ክፍል ሂሳብ መጽሄት ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2 MT Learning Goals by Measurement Topic (MT) በመለኪያ አርእስት የመማር ግቦች ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ ተማሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ... የእኩል ነው ምልክትን (=) ትርጉም ማብራራት። ለመደመርና ለመቀነስ የቆጠራ ስልቶችን መጠቀም። የማባዛት ስልቶችን በመጠቀም ከ20 ያነሱትን መደመርና መቀነስ። የእኩል ነው ምልክት ማለት በስተግራ ያለ መጠን ከበስተቀኝ ካለው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ነው። የእኩል ነው ምልክትን መረዳት የመጀመሪያ ደረጃ አልጀብራዊ አስተሳሰብ መሰረት ነው። የቃላት ፕሮብሌሞችን በዕቃዎች፣ በስዕሎች እና ቀመሮች በመጠቀም ለመፍታት ከ20 ያነሱትን መደመርና መቀነስ። ሶስት የሚደመሩ ቁጥሮች (addends) ያላቸው የቃላት ፕሮብሌሞችን (የድምር ውጤት ከ20 ያነሰ) በዕቃዎች፣ በስዕሎች እና ቀመሮች በመጠቀም መፍታት። ሶስት የሚደመሩ ቁጥሮች ያለው የመደመር ቀመር የሚደመሩ ቁጥሮች 7 + 2 + 1 = 10 ድምር Thinking and Academic Success Skills (TASS) አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች የአእምሮ/አስተሳሰብ ድፍረት የቋንቋ ቅልጥፍና ... ነው በሂሳብ ተማሪዎች የሚያደርጉት... ለአንድ ፕሮብሌም ወይም ለአንድ ሃሳብ በርካታ ምላሾች መፍጠር። የማባዛት ስልቶችን በመጠቀም የመደመርና የመቀነስ ቀመሮችን እና የቃላት ፕሮብሌሞችን መፍታት። በሂሳብ ውይይቶች ወቅት በመምህርና በዕድሜ አቻ ጓደኞች ስለተጠቀሙበት ስልቶች በመጠየቅ በንቃት መሳተፍ። ለአንድ የድምር ውጤት በርካታ ሶስት የሚደመሩ ጥንዶችን መለየት። አንድን ግብ ለመምታት አጠራጣሪን መቀበል ወይም ልማድን መፈታተን። ምንም እንኳ ስህተት የመሆን አጋጣሚ ሊኖር ቢችልም በራስ ፈቃደኛነት መልስ መስጠት። አንድ ስልት ወይም ፕሮብሌም ሲያምታታ እርዳታ መጠየቅና ለውጥ ማድረግ። ወጥነት ያላቸው የቃላት ፕሮብሌሞችን መፍጠርና መፍታት። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ5 ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የአንደኛ ክፍል ሂሳብ መጽሄት ማርክ መስጫ ወቅት 2፣ ክፍል 2 Learning Experiences by Measurement Topic (MT) በመለኪያዊ ርእስ የመማር ተሞክሮዎች ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... MT በመኖርያ ቤት፣ ልጃችሁ ማድረግ የሚችለው ... የሂሳብ ጨዋታዎችን በመጠቀም መደመርና መቀነስ መለማመድ። የቃላት ፕሮብሌሞችን በመፍታት ወቅት ያልታወቀውን (የጎደለውን ቁጥር) ለመወከል ቀመሮችን ከምልክት ጋር መጻፍ። ፕሮብሌም የመፍታት ስልቶች ምሳሌዎች መቁጠር በውደፊት/ወደኋላ አስር ማድረግ 8+3= 8ን ተናገር። ከዚያም የሚቀጥሉትን ሶስት ቁጥሮች ተናገር። የድምር ውጤቱ ( ቁጥሮች ተደምረው የሚገኘው ቁጥር) 11 ነው። ተማሪዎች ሁለት ቁጥሮችን ደምረው 10 የሚያደርጉበት ስልት። መደመር ለመለማመድ የመደመር ጨዋታ መጫወት። ጥቂት የዕቃዎች ክምችት (ጥራጥሬ፣ አንድ ሳንቲሞች፣ አሻንጉሊቶች ወዘተ) መሰብሰብ። ዕቃዎችን ለሶስት ቡድን መከፋፈል። የዕቃዎችን ስብስብ ለመወከል አንድ ቀመር ተናገር ወይም ጻፍ። ለምሳሌ፣ "እኔ 16 የባቄላ ፍሬዎች አሉኝ። የባቄላ ፍሬዎችን በ5፣ 7፣ እና 4 ቡድኖች ለመከፋፈል እችላለሁ። ስለዚህ፣ 5+7+4= 16።" ክምችቱን መልሰህ አንድ ላይ አድርግና ዕቃዎችን እንደገና በተለየ መንገድ ከፋፍላቸው። ሊደረጉ የሚችሉ ማጣመሮች ሁሉ እስከሚከነወኑ ድረስ ደጋግመው። 10 መስራትን ተለማመድ። ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ 10 ለመስራት የሚያስችሉ መንገዶች 11-3= 11ን ተናገር። ከዚያም ከ11 በፊት የሚመጡትን ሶስት ቁጥሮች ተናገር። ቀሪው/ልዩነቱ (ቁጥሮቹ ተቀንሰው የሚገኘው ቁጥር) 8 ነው። አንድ ስዕል መሳል ሁለት ጥንቸሎች በሳሩ ላይ ተቀምጠዋል። ሶስት ተጨማሪ ጥንቸሎች ዘለው መጡ። አሁን በሳሩ ላይ ምን ያህል ጥንቸሎች አሉ? ቀመር፡ = 2+3 መልስ፡ 5 ጥንቸሎች በጠረጴዛው ላይ አምስት አፕሎች ነበሩ። እኔ ሁለት አፕሎችን በላሁ። አሁን በጠረጴዛው ላይ ምን ያህል አፕሎች አሉ? ቀመር፡ 5-2 = መልስ፡ 3 አፕሎች ዕቃዎች፣ ስዕሎችና ቀመሮች በመጠቀም የድምር ውጤቱ ከ20 ያነሰ ሶስት መሉ ቁጥሮችን መደመር። አንድን የተወሰነ የድምር ውጤት የሚያስገኙ ሶስት የሚደመሩ ቁጥሮችን መለየት። 0 + 10 =10 6 + 4 = 10 1 + 9 = 10 7 + 3 = 10 2 + 8 = 10 8 + 2 = 10 3 + 7 = 10 9 +1 = 10 4 + 6 = 10 10 + 0 =10 5 + 5 = 10 ስለ ግላዊ ፍላጎት ወይም የዕለት ከዕለት ህይወት የሚመለከቱ የመደመርና የመቀነስ የቃላት ፕሮብሌምችን መፍጠርና መፍታት። ለምሳሌ፣ "እኔ በሳህኔ ላይ 8 የዶሮ ትናንሽ እንክብሎች (ችክን ናጌቶች) ነበሩኝ። እኔ ጥቂቶችን በላሁና አሁን 4 የቀሩ አሉኝ። እኔ የበላሁት ምን ያህል የዶሮ (ችክን) ናጌቶችን ነው?" ሶስት የሚደመሩ ቁጥሮችን በመጠቀም በኮምፒወተር ያለ መገልገያ ላይ በበርካታ መንገዶች መስራትን በመለማመድ ተመሳሳይ የድምር ውጤት ለማግኘት የአስተሳሰብ ድፍረት አድርግ፡ http://www.curriculumsuppoort.education.nsw.gov.au/countmein/children_ addition_wheel.html ለምሳሌ፡ 10= □ + □ + □ አንድ አማራጭ መልስ፡ 10=3+2+5 በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ5 ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs