Comments
Transcript
የአንደኛ ክፍል ሂሳብ ዜና መጽሄት የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት MT
የአንደኛ ክፍል ሂሳብ ዜና መጽሄት ማርክ መስጫ ወቅት 3፣ ክፍል 2 የመማር ግቦች በመለኪያ አርእስት (Learning Goals by Measurement Topic - MT) MT በአስር ቤት ቁጥርና ግብረቶች ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ ተማሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ... በመደመርና በመቀነስ መካከል ያለውን ግንኙነት አገልግሎት ላይ በማዋል ፕሮብሌሞችን መፍታት ። የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ከ20 በታች ባሉ ቁጥሮች መደመርና መቀነስ። ያልታወቀን (የጎደለ/የሌለ ቁጥር) በሁሉም ቦታ ሆኖ ቀመሮችን መፃፍና መፍታት። በዕቃዎች፣ በስዕሎች እና ቀመሮች በመጠቀም የቃላት ፕሮብሌሞችን ለመፍታት ከ20 ቁጥር ሳያልፉ መደመርና መቀነስ። አንድ ባለ 2-ቤት ቁጥር በዜሮ የሚያልቅ ባለ 2-ቤት ቁጥር ላይ መደመር። ከምሳሌዎቹ መካከል፡- 7 = 40 + 15 እና 25 + 30 = በ0 የሚያልቁ ባለ2-ቤት ቁጥሮች መቀነስ ከምሳሌዎቹ መካከል፡- 70-30 = እና = 40-20 ባለ 2-ቤት ቁጥር እና ባለ 1-ቤት ቁጥር መደመር። ከምሳሌዎቹ መካከል፡- = 45 + 2 እና 32 + 9 = አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች (Thinking and Academic Success Skills -TASS) ...ነው ጥረት/ተነሳሽነት/ብርታት ገንቢ ትንተና የጠቅላላውን ጽንሰ ሃሳብ መረዳትን ለማዳበር ወይም አዲስ ወይም ልዩ የሆነ ሙሉ ለመፍጠር የተለያዩ ከፍሎችን አንድ ላይ ማገጣጠም። በሂሳብ፣ ተማሪዎች የሚያደርጉት... በመደመርና በመቀነስ መካከል ያለውን ግንኙነት በመጠቀም ያልታወቀን (የጎደለ/የሌለ ቁጥር) መፍታት/ማግኘት። ያልታወቀን (የጎደለ/የሌለ ቁጥሮች) በሁሉም ቦታ ያሉባቸው የቃል ፕሮብሌሞች መፃፍና መፍታት። ኢላማ ላይ ያለ ድምር የሚያመጡ መደመር የሚችሉ በለ 2-ቤት ተደማሪዎች ማግኘት። የኢላማ ድምር፡- 54 ሊሆኑ የሚችሉ ተደማሪዎች፡- 10 እና 44 (10 + 44 = 54)፤ 30 እና 24 (30 + 24 = 54)፤ 40 እና 14 (40 + 14 = 54)፤ 50 እና 4 (50 + 4 = 54) አንድን ግብ ለመምታት ወይም አንድን ፕሮብሌም ለመፍታት በርትቶ መስራትና ውጤታማ ስልቶችን በስራ ላይ ማዋል፤ መሰናክሎችና ተፎካካሪ ጉዳዮች/ሃይሎች እየተቋቋሙ መቀጠል። በቀመር ውስጥ ያልታወቀውን (የጎደለ/የሌለ ቁጥር) በሚፈቱበት ወቅት የፅናት መኖር። ፈታኝ የሆነ የቃል ፕሮብሌም ለመፍታት አንድ ስልት እንዴት እንዳገዘ መግለፅ። አንድ ስልት አልሰራ ካለ ከመምህርና ከጓዶች ሀሳቦችን በበጎ ፈቃድ መቀበል። በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs የአንደኛ ክፍል ሂሳብ ዜና መጽሄት ማርክ መስጫ ወቅት 3፣ ክፍል 2 የመማር ተሞክሮዎች በመለኪያዊ አርእስት (Learning Experiences by Measurement Topic - MT) ት/ቤት ውስጥ፣ ልጃችሁ ... ግብረቶችና የአልጄብራ አስተሳሰብ MT ያልታወቀ ተደማሪ ፕሮብሌም ለመፍታት በመቀነስ መጠቀም። ለምሳሌ፣ 4 + = 9 የሚል ፕሮብሌም ሲቀርብ፣ ተማሪዎች 9 – 4 = የሚለውን በመፍታት ያልታወቀው ቁጥር "5" ብለው ይለያሉ። ከ10 በታች ባሉ ቁጥሮች የተዛመዱ የመደመርና የመቀነስ ቀመሮች መፍታት። ለምሳሌ፣ 5 = 2 + 3 ሲሰጥ 5 - = 3 በሚለው ያልታወቀው ቁጥር "2" መሆኑን ሁለቱም ቀመሮች የተዛመዱ በመሆናቸው ተማሪዎች ይለዩታል። የሆነ ባለ 2-ቤት ቁጥር እና በ0 የሚያልቅ ባለ 2-ቤት ቁጥር (10፣ 20፣ 30፣ ወዘተ) መደመር base32 + 20 = 52 10 blocks እና/ወይም Digiblocks የመሳሰሉ የቦታ-ዋጋ መለዋወጫ (place-value manipulative) በመጠቀም። በሂሳብ ግጥሚያዎች እየተጫወቱ በ0 የሚያልቁ ባለ 2-ቤት ቁጥሮች መቀነስ። ቦታ-ዋጋ መለዋወጫዎች (place50 = 70 – 20 value manipulatives) በመጠቀም በአስር ቤት ቁጥርና ግብረቶች ቤት ውስጥ ልጅዎ ማድረግ የሚችለው/የምትችለው... ባለ 2-ቤት ቁጥር በባለ 1-ቤት ቁጥር ላይ መደመር። ምሳሌ 1 (ተማሪ አንድ አስር መደረስ አያስፈልገውም) 29 = 24 + 5 ምሳሌ 2 (ተማሪ አንድ አስር መደረስ ያስፈልገዋል) 24 + 8 = ከ10 በታች የሆኑ ነገሮች (ቁልፎች፣ ሳንቲሞች፣ አሻንጉሊቶች) መሰብሰብ እና የነገሮቹን ድምር የሚወክል የመደመር ቀመር መፃፍ። ለምሳሌ፣ 7 ነገሮች ተመርጠው ከሆነ፣ ሊሆን የሚችል ቀመር 7 = 5 + 2 ነው። ከዚያም የተዛመደ የመቀነስ ቀመር (7 – 2 = 5) መፃፍ። በተለያዩ የነገር መጠኖች መደጋገም። ይህን ድርጣብያ በመጠቀም የተዛመዱ የመደመርና የመቀነስ እውነታዎች መለየት፡http://www.ixl.com/math/grade-1/related-addition-facts ባለ 2-ቤት ቁጥር መምረጥ። ከዚያ ቁጥር በመነሳት፣ በያንዳንዱ ዝላይ 10 እየደመሩ የዝላይ ጂምናስቲክ (jumping jacks) 24 34 44 54 መስራት። በሂሳብ ውይይት መሳተፍ። ዛህራ ሶስት ጊዜ መጣል። የመጀመርያዎቹን ሁለት ቁጥሮች በመውሰድ ባለ 2-ቤት ቁጥር መስራት እና ሶስተኛውን ቁጥር እንደ ተደማሪ መጠቀም። አስር መድረስ ፕሮብሌም ለመፍታት አስፈላጊ መሆን አለመሆኑን መወያየት። ለምሳሌ፣ 4 እና 6 በመጀመርያ ውርወራ ወጥተው ከሆነ፣ በ46 ቁጥር መጠቀም ይቻላል። በሶስተኛው ዙር 5 ከመጣ፣ የመደመር አረፍተነገር = 46 + 5 ይሆናል። = 46 + 5 በሚለው ቀመር፣ ስድስት አንዶች አምስት አንዶች ጋር ሲደመር 11 አንዶች ስለሚሆን አንድ አስር መደረስ ይኖርበታል። 1ኛ ዙር 2ኛ ዙር 3ኛ ዙር ባለ 2-ቤት የመደመር ፕሮብሌሞች ለመፍታ መስመር ላይ ባለ መገልገያ መጠቀም መለማመድ፡http://nlvm.usu.edu/en/nav/frames_asid_154_g_1_t_1.html?from=category_g_1_t_1.html የአስር አደራረስ 24 + 8 =32 በMCPS መምህራን በC 2.0 Summit 2013 የተፈጠረ ትርጉም Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs • Office of Curriculum and Instructional Programs